ድርጅቱ የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት አከባበርን አስመልክቶ ከአጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ወይይት አካሄደ! አዲስ አበባ ፤ መስከረም 10 ቀን 2018ዓ.ም

ድርጅቱ የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት አከባበርን በተመለከተ "በእምርታ እና ማንሰራራት የታጀበ ህዝባዊ በዓላትን በጋራ እናክብር" በሚል መሪ ቃል ከአጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ወይይት አድርጓል።

የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መስፍን አሰፋ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የመስቀል እና ኢሬቻ በዓላት ትውፊታቸውና እሴታቸውን ጠብቀው፤ በወንድማማችነት፣ እህትማማችትና በሰላም ተከብረው እንዲውሉ ሁሉም በሃላፊነት ድረሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡

ሰነዱን ያቀረቡት አቶ ካሳሁን ሙላት ሲሆኑ የውይይቱ ዓለማም ኢትዮጵያ በአያሌ ቅርሶችና እሴቶች የበለፀገች ሃገር መሆኗን፣ የመስቀልና የኢሬቻ በዓል በዩዮኒስኮ ከተመዘገቡ የማይዳስስ ቅርሶች ውሰጥ ሲሆኑ በመስከረም ወር በኢተየጵያ ብሄረሰቦች በልዩ ድምቀት የሚከበሩና በህዝቦች መካከል ይቅርታን፣ ሰላምን፣ የወንድማማችነትና እትማማችነት የሚታይበት የአደባባይ በዓላት መሆናቸውን አንስተዋል። እንዲሁም በዓላቱ ሲከበሩ በሠላም፣ በፍቅር፣ በወድማማችነትና እህትመማችነት መሆን እነዳለበት በመግለፅ የሚጠበቅብንን ማድረግ እንዳለብን ገልፀዋል፡፡

የድረጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ በማጠቃለያ እንደገለፁት የመስቀልና ኢሬቻ በዓላት ስናከብር እስቶቻቸውንና ትዉፊታቸውን ጠብቅው እንዲከበሩ በየአካባቢያችን ድርሻችንን አንድንወጣ ያሳሰቡ ሲሆን በዓሉን ስንከበር ዳግማዊ አደዋ የሆነውን የህዳሴ ግድባችንን በተባበረ ክንዳችን አጠናቀን ባስመረቅንበት ወቅት በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል ሲሉ ተናግረዋል።