ድርጅቱ አዲሰ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋራ። ጳጉሜ 5/13/2017 ዓ.ም _አዲስ አበባ ንግድ ሥራዎች ድርጅት።

የአዲስ አበባ ንግድ ሥራዎች ድርጅት የ2018 የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማዕድ አጋርቷል። ይህም ፕሮግራም እየተካሄደ የሚገኘው በዋና መስሪያ ቤት ፣ በለሚ እንጀራ ፣በብርሃን ዳቦ ፋብሪካ ፣በጉለሌ እንጀራ እና በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ነው።

የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መስፍን አሰፋ ተቋሙ ከአገልግሎት ስራው ባሻገር ማኅበራዊ ግዴታውን እየተወጣ እንደሚገኝ አንስተው ከዚህ በፊት በየጊዜው ለወገኖቻችን ማዕድ እንደምናጋራው ሁሉ ዛሬም የ2018 አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ ለወገኖቻችን ዠቨማዕድ ሰናጋራ ከፍተኛ ደስታ እየተሰማን ነው "ብለዋል ።

ድጋፊም አቅም የሌላቸውን እና በዝቀተኛ ገቢ ደረጃ ላላቸው ከ1,397 በላይ ለሚሆኑ ወገኖቻችን የምግብ ዱቄት፣ ዘይትና የመሳሰሉትን አቅርቦ ማዕድ በማጋራት ለወገኖቹ ያለውን አጋርነት አሳይቷል።