የድርጅቱ ራዕይ፣ ተልዕኮና እሴቶች
1.ራዕይ
በ2022 ዓ.ም በሀገሪቱ አቅርቦትና ፍላጎትን ለማጣጣም ሰፊ የገበያ ድርሻ ካላቸው ትርፋማ የልማት ድርጅቶች መካከል ግንባር ቀደም ሆኖ ማየት፤
የግብርናና ኢንዱስትሪ ምርቶችን ከሃገር ውስጥና ከውጭ ሃገራት ገዝቶ በማቅረብ፣ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ በማምረት፣ በማስመረት፣ ክምችት በመያዝ እና በከተማዋ ለሚገኙ የመሰረታዊ ሸማች ህብረት ስራ ማህበራት፣ ለአገልግሎት ሰጭ ተቋማት እና ለሸማቹ ህብረተሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ በማሰራጨት ገበያ ማረጋጋት ነው፡፡
- ታማኝነት (Integrity)
- ተጨባጭነት (Objectivity)
- መልካም ስም (Reputation )
- ተለዋዋጭነት (Flexibility)
- ተደራሽነት /Accessiblity/
- ፈጠራ /innovation
የአዲስ አበባ ንግድ ስራዎቸ ድርጅት ዓላማ/ተግባርና ኃላፊነት
- የተመረጡ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችንና መሠረታዊ ሸቀጦችን ከአገር ውስጥ እና ከውጭ አገር በቀጥታ ከአምራች ወይም እንደ አስፈላጊነቱ ከአከፋፋይ በተመጣጣኝ ዋጋ ገዝቶ በማሰራጨት በከተማ ውስጥ ገበያን ማረጋጋት፤
- የሰብል፤ አትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶችን በተመረጠ አኳኋን ማምረት፣ ማስመረት፤ መግዛትና ማሰራጨት፤ ክምችት መያዝ፤ በከተማ ውስጥ ለሚገኙ የተቋሙ መሸጫ ሱቆች፤ ሸማች ሕብረት ሥራ ማህበራት እና ለተመረጡ የህዝብ አገልግሎት ለሚሰጡ ተቋማት ማቅረብ፤
- በወቅታዊ የገበያ መረጃ ላይ ተመስርቶ ከየክልሉ የግብርና እና መሰረታዊ ሸቀጦች ግዥን መፈፀምና መሸጥ፤
- ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር ለንግድ የሚውሉ የተለያዩ ግዥዎችን ይፈጽማል፤ ይሸጣል፤
- በከተማው ዳርቻ እና በአጎራባች ክልል የአርሶ አደሩ የማምረት ፍላጎት እንዲያድግ ለግብርና ምርቶች አስተማማኝ ገበያ እንዲፈጠር እገዛ ማድረግ፤
- የድርጅቱ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን በሚሰጠው አቅጣጫ መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ተደራሽ፤ ተወዳዳሪና አትራፊ ሆኖ እንዲንቀሳቀስ እገዛ የሚያደርጉለትን የሰው ሃብት ማሟላት፤
- የቴክኖሎጂና ዘመናዊ ሥራ አመራር ግብዓቶችን ለማግኘት የሚያስችለው ኢንቨስትመንት መሳብም ሆነ በኢንቨስትመንት ላይ መሳተፍን ጨምሮ ጥናት በማካሄድ ሲፈቀድ ተግባራዊ ማድረግ፤
- የከተማ አስተዳደር ካቢኔ ሲፈቅድ ቦንድ መሸጥ፣ ዋስትና ማስያዝ፣ ከሀገር ውስጥ የገንዘብ ምንጮች የብድር ውል መደራደርና ሲፈቀድ መፈራረም፤
- ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎችን መሥራት፡፡
