የአዲስ አበባ ንግድ ስራዎች ድርጅት
Addis Ababa Business Trading Enterprise

  • Sine Up Now
  • መግቢያ
  • ስለእኛ
    • የዋና ስራ አስኪያጅ መልዕክት
    • የተቋሙ ታሪክ
    • ተልዕኮ፣ራዕይና እሴቶች
    • ስልጣንና ተግባር
    • ተቋማዊ መዋቅር
    • ሃላፊዎችና ዳይሬክተሮች
    • አግኙን
  • ዜና እና ሚዲያ
    • ትኩስ ዜናዎች
    • ፎቶዎች
    • ቪዲዎች
  • ማስታወቂያ
    • ማስታወቂያዎች
    • ክፍት የስራ ቦታ
    • ጨረታዎች
  • መረጃዎች
    • አዋጆች
    • መመሪያዎች
    • ሰነዶች
    • ጥናቶች
  • አግኙን
  1. Home
  2. About Us

About Us

  1. Home
  2. Message

የድርጅቱ ታሪካዊ አመሰራረት

መግቢያ

ሃገራችን ኢትዮጵያ የልማት ድርጅት ማቋቋም ከጀመረች በርካታ ዓመታት አስቆጥራለች፡፡ መንግስት በቀጥታ በማይገባባቸው ዘርፎች፣የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት እና የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ፣ በርካታ ስራዎች ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ስለሆነም ከአዲስ አበባ ንግድ ስራዎች ድርጅት ጋር ተመሳሳይ ይዘትና ባህሪት ያላቸው በርካታ ልማታዊ ድርጅቶች ተመስረተዋል እነርሱም ኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ፣ የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት ግብዓት አቅራቢ ድርድት፤ ኢትፋሩት እና በክልሎች መሰል ተቋማት በማቋቋም ወደ ስራ ከገቡ በርካታ ዘመንናት ተቆጥሯል ፡፡ ስለዚህ ከእነርሱ ልምድ በመውሰድ ከተማ አስተዳደሩ የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት በጥብቅ ዲሲፕሊን መምራትና ውጤት ማስመዝገብ አስፈላጊ ነው፡፡፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልማት ድርጅቶች የሚመሩበት ሁኔታ ለመወሰንና ለማቋቋም ባወጣው ደንብ ቁጥር 14/1991 በከተማ አስተዳደሩ ባለቤትነት የማምረት፣ የማከፋፈል፣ አገልግሎት ለመስጠት የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን ባወጣው አዋጅ ቁጥር 84/2016 መሰረት 10 የልማት ድርጅቶች ያቋቋመ ሲሆን ከዚህ ውስጥ አንዱ የአዲስ አበባ የንግድ ስራዎች ድርጀት በደንብ ቁጥር 152/2015 ዓ/ም በመመስረት የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት ፣መንግስት የማያቀርባቸውን ምርትና አገልግሎቶች በጥናት በማረጋገጥ የመፍትሄ ሃሳብ በማቅረብ የተለያዩ የምርት ውጤቶችን ከተማ አስተዳደሩ በሚወጣው ታሪፍ መሰረት ለህብረተሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ(በትንሽ ትርፋ) በማቅረብ የተገልጋዩን እርካታ ማሳደግ የድርጅቱ ዋነኛው ተግባር ነው፡፡

ታሪካዊ አመሰራረት

የአዲስ አበባ የንግድ ሥራዎች ድርጅት በመነሻ ካፒታል ብር 7.25 ቢሊየን ሐምሌ 15/2015 ዓ/ም በደንብ ቁጥር 152 ተመሰረት፡፡ ድርጅቱ ለከተማ አስተዳደር ሸማቹ ህብረተሰብ የግብርና፣ የኢንዱስትሪ ምርቶችን እና የንግድ እቃዎችን በቀጥታ ከአምራቹ ጋራ የገበያ ትስስር በመፍጠር በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ አገልግሎት እንዲሰጥ የተቋቋመ ድርጅት ነ፡፡ በመጀመሪያ 1 አመት ጊዜ ውስጥ ወደ ብር 85,226,825.22 ብር በላይ ያልተጣራ ትርፍ ያገኘ ሲሆን ድርጅቱ ከከተማ አስተዳደሩ በተሰጠው ድጋፍ ቢሮና መጋዘን ያለው ሲሆን ለድጋፍና ክትትልም ምቹ ስፍራ ላይ ይገኛል፡፡ ድርጅቱ በደንብ ቁጥር 152/2015 ዓ.ም ቢቋቋምም ወደ ስራ የገባው ሚያዝያ 2016 ዓ.ም ነው፡፡ ድርጀቱ የመጀመሪያ ስራ አሰኪያጅ በሆኑት በአቶ መስፍን አሰፋ እየተመራ የገኛል፡፡

በድረጅቱ የሚተዳደሩ ፋበሪካዎች

  • የብርሃን ምግብ ማቀነባበሪ ፋብረካ/ የማኑፋክቸሪግ ዘርፍ፣
  • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የነዋሪዎቿን የኑሮ ጫና ለመቀነስ የዳቦ ምርት አቅርቦት፣ ጥራትና ተደራሽነት አነስተኛ በመሆኑ ለተጠቃሚው ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ እንዲቻል ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ የዳቦ አቅርቦት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት፤ የህብረተሰቡን ገቢ ባገናዘበ ተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን ለማቅረብ፣ የኑሮ ውድነቱን በመቀነስ የህዝብን የዳቦ ፍላጎት ምላሽ የሚሰጥ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ፣ በራሱ ገቢ የሚተዳደር ተቋም መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገነቱ በ2014 ዓ.ም በቀዳማይ እመቤት ጽ/ቤት ተነሳሽነት የተገነባ ነው፡፡ ሆኖም ድርጅቱ በ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ የንግድ ሥራዎች ድርጅት ስር እንዲተዳደር ከተማ አስተዳደሩ ውሳኔ መሰረት ወደ ስራ ተገብቷል፡፡ በመሆኑም ይህ ድርጅት ሳይስራ በመቆየቱና የዳቦ ፋብሪካው ላይ በረካታ ችግሮች /ጥገና የሚስፈልጋቸው ማሽኞች አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በመለየት በአጭር ጊዜ፣ በመካከለኛ እና በረጃም ጊዜ የሚፈቱ ችግሮች ተላይተዋል በአጭርጊዜ ጥገና የሚስፍልጋቸውን የዳቦ ምርት ለማመረት የሚስፍልጉ ቁሳቁሶችን በመለየት ማስጠገን፣ የዱቄት ፍብርካ ተከላ ማካሄድና ማስጀመር ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ እንደ ውሃ ጉድጓድ ቁፍሮ፣ መጠባበቂያ ጀኔሬተር፣ ዴቄት መግፍያ ማሽን ፣ ሃርድዌርን ወደሶፍት ሚቀይር ማሽን ፣የበረዶ መስሪያ ማሽን ፣ ኦቫን እና የመሳስሉ ችግሮችን በመፍታት በመሉ አቅሙ ለማስራት አዲስ አበባ ንግድ ስራዎች ድርጅት እየተጋ ይገኛል ፡፡
  • ጉለሌ እንጀራ ፋብሪካ፣
  • ለሚ እንጀራ ፋብሪካ፣
  • .

    ስለእኛ

    Logo
    የአዲስ አበባ ከተማ የሀገሪቱ ርዕሰ መዲና፣ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እና የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎችና ዓለ... Read More

    ለፈጣን መረጃ

    • መግቢያ
    • ስለእኛ
    • ዜናዎች
    • ማስታወቂያ
    • አግኙን

    በዚህ ያግኙን

    • ፒያሳ እሪበከንቱ
    • ከኢትዮ ሴራሚክስ ወረድ ብሎ
    • EMA Tower 16ኛ ፎቅ
    • ስልክ: +251967686058/51
    • ኢሜል: aabtradingenterprise@gmail.com

    © 2025 AABET. All Rights Reserved

    Social Midea