ሰነዱ አቅራቢ አቶ ካሳሁን ሙላት በዋናነት ያነሱት የህዳሴ ግድብ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በተባበረ ክንዳችን አጠናቀን ማስመረቃችን የድል ምልክትና ዳግማዊ አደዋ መሆኑን ለማስመዝገብ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
ሰነዱን መነሻ በማድረግ የድርጅቱ ሰራተኞች ውይይት ያደረጉ ሲሆን ግድቡ ተጠናቆ በመመረቁ ደስታቸውን ገልፀል፡፡
የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መስፍን በማጠቃለያ በድጋሜ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕከት ያስተላለፉ ሲሆን በአደዋ የተደረገውን ድል የህዳሴ ግድብን በማጠናቀቅና ማሰመረቅ ድሉን የደገምነው ሲሆን ግድቡ የይቻላልን መንፈስ ያላበሰና በኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል ወንድማማችነትን ፣ አብሮነትን እና ላመኑበት ነገር ያላቸውን ጽናት የሚያሳይ መሆኑን ገልፀዋል።
