እንኳን ደህና መጡ!!

የአዲስ አበባ ከተማ የሀገሪቱ ርዕሰ መዲና፣ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እና የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎችና ዓለማቀፋዊ ድርጅቶች መቀመጫ እንደሆነች የሚታወቅ ሲሆን ከተማዋን አለም አቀፍ ተወዳዳሪ፣ ሳቢና ማራኪ ለማድረግ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፡፡ የከተማዋን ነዋሪ ህብረተሰብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄን ምላሽ በመስጠት መዲናዋን ለነዋሪዎቿ ምቹና ተመራጭ እንድትሆን ለማድረግ የከተማው አስተዳደር በርካታ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ሆኖም በየጊዜው እያደገ ከመጣው የነዋሪው ህብረተሰብ ፍላጎት የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት ተቋማት የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ውስንነት የተነሳ በከተማው አስተዳደር ሰፊ ችግሮች እንደሚታዩ በተለያዩ ጊዜያት ከሚቀርቡ ሪፖርቶች እና በተለያዩ አካላት ከተሰሩ ጥናቶች ማረጋገጥ ማረጋገጥ የሚቻል ነው፡፡እነዚህ በከተማዋ በሰፊው የሚስተዋሉ ችግሮች ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮችን የሚካትቱ ናቸው፡፡ በመሆኑም አስተዳደሩ እነዚህን ችግሮች በመፍታት ከተማዋን ለኑሮ፣ ለስራ እና ለመዝናኛ ስፍራ ምቹና ተመራጭ ከተማ ለማድረግ በርካታ ተግባራት በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
አቶ መስፍን አሰፋ
ዋና ስራ አስኪያጅ
Showing 5 of